የኢንስቲትዩቱ ማኔጅመንት አባላት ፣ ባለድርሻ አካላትና የዞኑ አስተዳደር በኢትዮጵያ ከሚገኙ ተራሮች ሁለተኛው ትልቁ (4377ሜትር ከባህር ጠለል በላይ) የሆነውን ሳናቴ
(ቱሉ ዲምቱ )ተራራን ጎበኙ።”ቱሪዝም ለዘላቂ ለውጥ” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ያለው የዓለም ቱሪዝም ቀንን ኢንስቲትዩቱ በኦሮሚያ ክልል በባሌ ዞን አስተዳደር ሮቢ ከተማ እያከበረ ይገኛል።የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ተፈጥሯዊ መልክዓ ምድሩ እና በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኘው የቀይ ቀበሮ መኖሪያ እንዲሁም እነ ድኩላ፣ ኒያላ የሚገኙበት የቱሪስትን ቀልብ የሚስብ ተመራጭ የመዳረሻ ስፍራ ነው። የበዓሉ አከባበር ነገ በተለያዩ ዝግጅቶች ነገም ይቀጥላል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ ።
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et

Recent Comments