ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ባለፈው አንድ ዓመት ሲያደርግ የነበረውን የኢንስቲትዩቱ አግልግሎት ሪፎርም ዝግጅት ምዕራፍን በማጠናቀቅ ወደ ተግባር መግባቱን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ገለጹ ።

የሪፎርም ሥራው ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት፣ ለስልጠና ለምርምርና ማማከር ሥራውና አጠቃላይ ለተቋሙ የተሰጡ ተልዕኮዎችን ለመፈጸም ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ የምንሰጣቸው አገልግሎቶች የደምበኞችን እርካታ የሚጨምር መሆኑን እያረጋገጥን እንቀጥላለን ብለዋል።
በዝግጅት ምዕራፍ የተሰሩ ሥራዎችን ገለፃ ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች በሚመደቡበት ሥራ መደብ ላይ ምዘና የሚደረግ ሲሆን ተከታታይነት ያለው ድጋፍም ይደረጋል ብለዋል።
የሥራ አመራርና አስተዳደር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ በበኩላቸው በኢንስቲትዩቱ ምቹ የሥራ ሁኔታን ለመፍጠር ጥራት ያለው የተቋም እድሳት ተደርጓል፤ ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ የውስጥ መመሪያዎች ተዘጋጅተዋል፣ የስልጠና ጥራትን ከመጠበቅ አኳያም ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የመንግስት አገልግሎት ሪፎርምን ከሚተገብሩ ስምንት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ኢንስቲትዩቱ ተጠሪ የሆነበት ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አንዱ ነው።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et