ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልየሥራና ክህሎት ሚኒስትር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ የለውጡን 7ኛ ዓመት በማስመልከት “ትናንት፣ ዛሬና ነገ ለኢትዮጵያ ልዕልና” በሚል መሪ ሃሳብ ውይይት አካሂደዋል። በመድረኩ ባለፉት ሰባት ዓመታት በፖለቲካ፣

ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ዲፕሎማሲያዊ መስኮች የነበሩ ፈተናዎችና የተገኙ ድሎች ላይ ያተኮረ ሰነድ በሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ መድረኩ ባለፉት ሰባት ዓመታት እንደ ሀገር የገጠሙ ፈተናዎችና የተገኙ ድሎች ላይ ሁሉም ሠራተኛ መረጃ ኖሮት ለላቀ ተልዕኮ እንዲዘጋጅ ለማድረግ አልሞ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ስርዓታዊና መዋቅራዊ በሆኑ የውስጠ ድርጅትና ተያያዥ ምክንያቶች የመጣው የለውጥ መንግስት እንደ ሀገር ሲወርድ ሲወራረድ የመጣውን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊና መሰል የትውልዶች ጥያቄን ለመመለስ በቁርጠኝነት እየሰራ ነው፡፡
በዚህም ኢኮኖሚው ከነጠላ እይታ ወጥቶ ወደ ብዝሀ ዘርፍ እንዲያተኩርና ሀገረ መንግስቱ የፀና መሰረት እንዲኖረው ተቋማትን ነፃና ገለልተኛ አድርጎ መገንባት የሚያስችል ሪፎርም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡
የፖለቲካ ስነ-ምህዳሩን ለማስፋትም አንድም ወንበር በምርጫ ካላሸነፈ ፓርቲ ጋር ስልጣን አጋርቶ በመስራት አዲስ የፖለቲካ ባህል ለመገንባት መንግስት ረዥም ርቀት መሄድ እንደቻለም አውስተዋል፡፡
እንደ ሀገር አሁንም የተጣሉ ሀሳቦችና ያልታረቁ ፍላጎቶች ቢኖሩንም ችግሮቻችን በንግግር የማይፈቱ አይደሉም ያሉት ክብርት ሚኒስትር መንግስት እነዚህ ፍላጎቶች በድርድር፣ በውይይትና በምክክር መፈታት ይኖርባቸዋል ብሎ መሰረተ ሰፊ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
በዚህም የትጥቅ ትግል የመረጡትን ሳይቀር አሁንም ድረስ ያልተቋረጠ የሰላም ጥሪ እያቀረበላቸው እንዳለ ገልፀዋል፡፡
ላለፉት ሰባት ዓመታት ያለማቋረጥ እየተስተጋባ ያለው የሰላም ጥሪ መንግስት ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ካለው ጽኑ ፍላጎት የመነጨ እንደሆነም አመላክተዋል፡፡
ባለፉት ሰባት ዓመታት የተሰሩ ስራዎች ኢትዮጵያን ወደፊት የሚወስዱና ለመጭው ትውልድ የምትበቃ ሀገር እንድትሆን ማድረግ የሚያስችል እውነታን መፍጠር ላይ ያተኮረ እንደሆነ ክብርት ሚኒስትር ገልፀዋል፡፡
በብዙ ወጀብ መሃልም ሆነን የሰባት ዓመት ጉዟችን እዚ ካደረሰን የማምረት አቅማችንን ከጨመርን በማይቋረጠው የህዳሴ ጎዟችን የኢትዮጵያን ልዕልና እናረጋግጣለን፡፡
ለዚህም ሁሉም ተቆጥሮ ከተሰጠው ሥራ በላይ እየሰራ በየተሰማራበት ለገር ግንባታው የበኩሉን ሚና መወጣት ይኖርበታል ብለዋል፡፡
ሐምሌ 24/2016 ዓ.ም
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት https://lmis.gov.et