የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የሥራ አመራር ቦርድ አባል የሆኑት ዶ/ር ፍትህ ወ/ሰንበት እ.ኤ.አ በ29/03/2025 በኮትዲቯር አቢጃን ለአምስተኛ ጊዜ በተካሄደው የኢንተርናሽናል አፍሪካን ቢውልደርስ ኮንፈረንስ ፕሮግራም የደብል ኦስካር ተሸላሚ በመሆናቸው የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አመራርና ሰራተኞች የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡
በሽልማት ፕሮግራሙ መቀመጫቸውን በአቢጃን ያደረጉ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች፣ በምዕራብ አፍሪካ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት የማህበር መሪዎች እና በተለያዩ ዘርፍ ዕጩ የነበሩ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች መገኘታቸውን ልዩ ልዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ገልጸዋል።ዶ/ር ፍትህ የሴንትራል ያማረች ሀዋሳ ሆቴል፣ የኢትዮጵያ ሆቴል እና ቱሪዝም አሰሪዎች ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት እንዲሁም የኢትዮጵያ እና የምስራቅ አፍሪካ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ሆነው ያገለግላሉ፡፡ለሽልማት የበቁት በሲዳማ ክልል በሀዋሳ ለሰሯቸው ኤንቨስትመንቶች፣ ከፍተኛ የሆነ ማህበራዊ ጉዳይ (Corporate Responsibilies) እና በተለያዩ ወቅት ባገኟቸው የሀገር ውስጥ ስኬቶች እንዲሁም በሀገር አቀፍ እና አህጉር አቀፍ የሆኑ አበርክቶዎች እንደሆነ ተገልጿል።
በድጋሚ እንኳን ደስ አለዎት ፡፡
የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት!
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et

Recent Comments