ቱ ማ ኢ ህዳር 20/2018 ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የሆቴልና ቱሪዝም ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር ስልጠና የ2017 ዓ ም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ መድረኩን ሲከፍቱ እንደገለፁት በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ የትብብር ስልጠና ጉልህ አስተዋጽኦ የነበራቸው ከ 140 በላይ ድርጅቶች የተሳተፉበት መድረክ መሆኑን ጠቅሰው
በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ በንድፈ ሃሳብና በተግባር የተደገፈ ስልጠና በመስጠት ሰልጣኞችን ማብቃት እንደሚያተኩር ገልጸዋል። ለዚህም ከኢንደስትሪው ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀራርቦ በመስራት ኢንስቲትዩቱ እድለኛ መሆኑን የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሩ
በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ለትብብር ስልጠና ከተላኩት ሰልጣኞች 99 በመቶ የሚሆኑት ሰልጣኞች የተሳካ ስልጠና እንዳገኙ ገልጸዋል።
የስልጠናና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት እንደተናገሩት በ2017 ዓ.ም በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ እንደባለድርሻ ስንጠራችሁ በመገኘት ሰልጣኞቻችንን ስንልክ እየተቀበላችሁ ዘመኑ የሚፈልገውን ባለሙያ ለማፍራት ያደረጋችሁት ጥረት የሚበረታታና የሚያስመሰግን ነው ብለዋል።
የተቋሙ ቮኬሽናል ጋይዳንስ ካውንስልንግ እና የትብብር ስልጠና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ዲን አቶ ታደሰ ሞላ በበኩላቸው የውይይቱ ዋና ዓላማ የኢንዱስትሪ ትብብር ስልጠና በሆቴል እና በቱሪዝም ዘርፍ ያለበትን ደረጃ መገምገም እና ቀጣይ ሥራዎችን በጋራ ለመስራት ማቀድ እንደሆነ ገልጸዋል።
በ2017 በጀት ዓመት ለትብብር ስልጠና ሰልጣኞችን ከተቀበሉ ሆቴሎችና ቱሪዝም ተቋማት አያ ሆቴል፣ ጊዮን ሆቴል ፣ ኤልጌል ሆቴልና ስፓ ፣ ከአዲስ አበባ ሙዚየም እና ኢትኖግራፊክ ሙዚዬም ስለትብብር ስልጠናው የነበረውን ሂደት ገለፃ አድርገዋል።
በመጨረሻም የተቋሙ የ10 ዓመት ፍኖተ ካርታ ቀርቦ ከተሳታፊዎች ግብዓት የሚሆኑ ሃሳቦች ተሰጥቷል።
መድረኩ በነገም የሚቀጥል ይሆናል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/


Recent Comments