ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በዓለም ቅርስነት በተመዘገበው የጥያ ትክል ድንጋይ ለቱሪስት አገልግሎት በመሰረታዊነት የሚያስፈልጉ መረጃ ዴስክ፣ የሥጦታ እቃዎች መሸጫ፣ ቱሪስት የሚያርፍበት መለስተኛ ካፌ እና መፀዳጃ ቤት ሊያሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ በሚሰራው አገልግሎት ሰጪ ግንባታ ላይ የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ውይይት የተደረገ ሲሆን ኢንስቲትዩቱ በስልጠና፣
በጥናትና ምርምር፣ ማማከር እና ማህበረሰብ አገልግሎትን እየሰጠባቸው ከሚገኙ መዳረሻዎች መካከል ጥያ አንዱ በመሆኑ የሚገነባው አገልግሎት ሰጭ ማዕከል ለጎብኝዎች ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር እንደሆነ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ገልጸዋል።
ዘንድሮ በተለያዩ መዳረሻዎች ላይ መሰል ሥራዎችን ለመስራት ታቅዶ የነበረ መሆኑን የገለፁት የኢንስቲትዩቱ የጥናት ምርምር እና ማማከር ዘርፍ ም/ዋ/ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም በተለይ የጥያ ትክል ድንጋይ የቱሪስት መስህብ በቅርበት አብሮ እየሰራ የነበረ መሆኑን ገልጸው የሚሰራው አገልግሎት ሰጪ ለአካባቢው ወጣቶች ለሥራ ዕድል ፈጠራም የበኩሉን አስተዋፅኦ ያደርጋል ብለዋል። ቅርሶች አካባቢ ተመሳሳይ መረጃ መስጠት ላይ ክፍተት መኖሩን ያነሱት አቶ ይታሰብ ይህ ሲጠናቀቅ ጎብኝዎች ስለ ቅርሱ መረጃዎችን የሚያገኙበትና እረፍት የሚወስዱበትም ይሆናል ብለዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et

Recent Comments