ኢንስቲትዩቱ በኢስትሪፕ ፕሮጀክት የተከናወኑ ሥራዎች ሪፖርት ለአማካሪ ቦርዱ አቀረበ።ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በ2017 በጀት ዓመት በኢስትሪፕ(EASTIP) ፕሮጀክት የተከናወኑ ሥራዎች ሪፖርት እና የቀጣይ በጀት ዓመት እቅድ ለአማካሪ ቦርዱ አቀረበ ።የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ በፕሮግራሙ መክፈቻ እንደተናገሩት አማካሪ ቦርዱ በጥናትና ምርምር፣ በትብብር ስልጠና ፣ በሥርዓተ ትምህርት ዝግጅት እገዛው ላቅ ያለመሆኑን እንስተዋል፤ ምስጋናም አቅርበዋል።
በመቀጠል የአማካሪ ቦርዱ ሰብሳቢ አቶ መልካሙ መኮንን ኢንስቲትዩቱ በፕሮጀክቱ አማካኝነት በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን እና በሪፖርቱ ያልተከናወኑ የምንላቸው ላይ በቀጣይ አትኩረን እንሰራለን ብለዋል።
የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ አብርሃም ለገሰ ባቀረቡት ሪፖርት በበጀት ዓመቱ ከታቀዱ አበይት ሥራዎች የስልጠና ጥራት የሚያመጡ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ፣ የባህላዊ ምግብ ጥናት በሀገሪቱ በአራቱም አቅጣጫዎች መከናወናቸው፣ የኢንስቲትዩቱ የተመራቂ ተማሪዎች የሥራ ስምሪት ጥናት ፤ሌሎች ከሪፎርም ጋር ተያያዥ የሆኑ ሰነዶች ዝግጅት እንዲሁም የመማሪያ ክፍሎችና የተግባር ስልጠና ወርክሾፖችና የአስተዳደር ክፍሎች እድሳት ከፍተኛ አፈፃፀም እንዳላቸው ገልፀዋል።
በመጨረሻም የአማካሪ ቦርዱ አባላት በቀረበው ሪፖርትና እቅድ ባደረጉት ውይይት የዲጂታል ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ ስልጠናን ተደራሽ ስለማድረግ፣ በዘርፉ የሚሰጠውን ስልጠና ፣ ከደረጃ ስድስት እስከ ስምንት (በዲግሪ ፣በማስተርስና በፒኤችዲ ደረጃ ማሳደግ እንደሚገባ ይኸም የእቅዱ አካል እንዲሆን ሃሳብ ሰጥተዋል።
ከአባላቱ በቀረበው ሃሳብ መሠረት ኢንስቲትዩቱም የስልጠና አቅምን በማሳደግ በመጪው 2018 ከደብረብርሃን ዩንቨርሲቲ ጋር በስልጠና ዙሪያ አብሮ ለመስራት መታቀዱ ተገልጿል።
ኢንስቲትዩቱ ኢስትሪፕ EASTRIP ፕሮጀክትን ዘግይቶ የተቀላቀለ ተቋም ነው።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et

Recent Comments