ቱ ማ ኢ ህዳር 21/2018 ዓ ምቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በሆቴልና በቱሪዝም ዘርፍ የትብብር ስልጠና ለሚሰጡ የኢንዱስትሪ ባለቤቶች እና ባለሙያዎች ጋር በተካሄደ የምክክር መድረክ እንደተገለጸው ኢንስቲትዩቱ ለትብብር ስልጠና የሚልካቸውን ሰልጣኞች በየጊዜው መገምገም እና መረጃ መለዋወጥ ጥሩ ተሞክሮ መሆኑ ተገልጿል።
የኢንስቲትዩቱ የሥልጠናና አቅም ግንባታ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት እንደተናገሩት ለትብብር ስልጠና የሚላኩ ሰልጣኞች በየደረጃው እየሰለጠኑ ባሉበት የሙያ መስክ መመደብና ያሉበትን ደረጃ በሚመጥናቸው ነጥብ መስጠት እንደሚገባ ገልጸዋል።
ኢንስቲትዩቱ ከጊዜ ወደጊዜ የአሰራር ሥርዓቱን እያዘመነ የክትልና የግምገማ ስርዓቱንም እያሳደገ እንደመጣም ለዚህም የቮኬሽናል ጋይዳንስና ካውንስሊንግ ዲን ጽ/ቤት ተቋቁሞ በጥብቅ ክትትል እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከመደበኛው ስልጠና ባሻገር በሙያው ራሳቸውን ማሳደግ ለሚፈልጉ፣ እንዲሁም በሌላ የሙያ መስክ ላሉ በማታ እና በቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በአጫጭር የስልጠና ዘርፎች ስልጠና እየሰጠ መሆኑን የአጫጭርና የማታ ስልጠና ማስተባበሪያ ዲን አቶ ዳንኤል በቀለ የገለጹ ሲሆን በዲግሪ ደረጃ የተከፈቱ የኢቨንት ማኔጅመንትእና ኩሉናሪ አርት ስልጠና ፈላጊዎች አሁንም መሰልጠን የሚችሉ መሆኑን ፤ በአጫጭር ስልጠና የዌልነስና ስፓ ስልጠናም ስርዓተ ትምህርት ተቀርፆለት ወደሥራ መግባቱን አብራርተዋል።
በአጫጭር ስልጠና ሁሌም ምዝገባ ሁሌም ስልጠና አለ።
በመጨረሻም ከትብብር ስልጠና ጋር በተያያዘ የክትትል ሰነዶች አሞላል ዙሪያ በአቶ ሳለአምላክ ፋንታ መረጃ ተሰጥቶ የምክክር መድረኩ ተጠናቋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/


Recent Comments