ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ በሆቴልና ቱሪዝም ሙያዎች በማሰልጠን፣ የማማከከር አገልግሎት በመስጠትና ለዘርፉ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር ሥራዎችን በማካሄድ ለሀገራችን ቱሪዝም እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እየተወጣ ይገኛል፡፡
ኢንስቲትዩቱ የተሰጡትን ተልዕኮዎች በሚገባ ለመወጣት የተለያዩ የሪፎርም ሥራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል፡East Africa Skills for Transformation and Regional Integration Project (EASTRIP) የቢሮዎች እድሳት፣ የስልጠና ክፍሎችን፣ ወርክ ሾፖችን ማደስና ግብዓት ማሟላት፣ የህጻናት ማቆያ፣ የሸማቾች ህብረት ሥራ የመሳሰሉት ምቹ የሥራ ከባቢን መፍጠርና የስልጠና አሰጣጡ በተግባር የተደገፈ በዘመናዊ መሳሪያዎች እንዲሟላ አስፈላጊው ሁሉ ለማሟላት ጥረ ተደርጓል፡፡ እንዲሁም በዘርፉ ጥናቶችን ለማካሄድ የነበሩ ክፍተቶችን ለመሙላት አስችሏል፡፡
መንግስት የሚኒስቴር መ/ቤቶችን ሪፎርም ለማድረግ ለሙከራ ትግበራ ከተመረጡት አንዱ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት በመሆኑ ኢንስቲትዩቱ ከሰነድ ዝግጅት እስከ ትግበራው ድረስ በርካታ ሥራዎችን አከናውኗል፡፡ ዓለም አቀፍ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ISO 21001/2018 መሰረት ተግባራቱን እያከናወነ ይገኛል፡፡
ኢንስቲትዩቱ በጀመራቸው የለውጥ ሥራዎች የሚጠበቀውን ውጤት ከማምጣት ባሻገር ቀጣይነት እንዲኖረው አበክሮ ይሰራል፤ ይህንንም ተሞክሮ የተለያዩ ተቋማት እያካፈለ ይገኛል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et

Recent Comments