የሀገራችንን ቱሪዝም ዘላቂነት ለማረጋገጥ የኢትዮጵያ ሆስፕታሊቲ አገልግሎት ደረጃ ሊኖር እንደሚገባ ተገለጸ ።የቱሪዝም ዘርፉን እንቅስቃሴ ዘላቂነት በማረጋገጥ ከዘርፉ ተጠቃሚ ለመሆን በሁሉም ሆቴሎችና የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ተቀራራቢ አገልግሎት ለመስጠት ሀገር አቀፍ የሆስፕታሊቲ አገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ ሊኖር እንደሚገባ የኢንስቲትዩቱ የጥናት ምርምርና ማማከር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ሥዩም ገለጹ ።
ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ሀገር አቀፍ የዘርፉ አገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ ዝግጅት ላይ ከሆቴል ሥራ አስኪያጆች ጋር ባደረገው ውይይት ላይ መልዕክት ያስተላለፉት አቶ ይታሰብ እንደ ሀገር የሆስፕታሊቲ ዘርፉ አገልግሎት አሰጣጥ የማይመሳሰል መሆኑን ገልጸው የሚቀራረብ አገልገሎት ካልተሰጠ ከዘርፉ የሚጠበቀውን ያህል ጥቅም ማግኘት አይቻልም ብለዋል
መነሻ ሰነዱን ያቀረቡት አቶ ሳህሌ ተክሌ ጎብኚ ከአየር መንገድ ጀምሮ እስከ መዳረሻ እና ወደ ሀገሩ እስኪመለሱ ድረስ ያለው ኢትዮጵያዊ የመስተንግዶ ባህል የተላበሰ አገልግሎት መስጠት ይገባል ብለዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ የጀመረው አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፣ የሀገር ውስጥ ጉብኝዎችንም ታሳቢ ያደረገ ደረጃ እንዲዘጋጅ ሃሳብ ሰጥቷል።
ይህን ግንዛቤ ለመፍጠር የሚዲያ ሚና ሊታይ እንደሚገባ የገለጹት ተሳታፊዎች እንደሌሎች የሀገራችን ህጎች የቱሪዝም ዘርፍ ህግም ቢኖር ተፈጻሚነቱን ከፍ ማድረግ እንደሚየፈቻል ገልጸዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et

Recent Comments