የባህል ምግቦች ለሥራ ዕድል ፈጠራ የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ በስልጠና መደገፍ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በ2017 ዓ.ም ካደረጋቸው ጥናትና ምርምሮች መካከል የባህል ምግቦችን ለሥራ እድልና ለኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የሚያሳይ ጥናት ቀረበ፡፡ ጥናቱን ያቀረቡት አቶ አህደር ጠና በአስር የክልል ከተሞች ላይ በተደረገ ጥናት ከ14 ሺህ በላይ ሰዎች በባህል ምግብ ዝግጅት ሥራ ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

በዚህ ሙያ ተሰማርተው የሚገኙ አብዛኛዎቹ በባህላዊና ከቀደሙ እናቶች በቀሰሙት ልምድ መሆኑን የገለጹት አቶ አህደር እንደ ሀገር ካለን የባህል ምግቦች ስብጥር ከዚህም በላይ ለማሳደግ ስልጠናዎችን መስጠት፤ ሥራ ለመጀመር የሚያስችል የመጀመሪያ ካፒታል የፋይናስ አቅራቢ ተቋማት እንዲያመቻቹ ፣ የባህልና ቱሪዝም ቢሮዎች፣ የሥራና ክህሎት ቢሮዎችና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት በመቀናጀት ዘመናዊ በሆነ መልኩ የባህል ምግችቦችን ለገበያ ማቅረብ እንደሚቻል ባቀረቡት ጥናት አመላክተዋል፡፡
ከባህል ምግቦቻቸው ተጠቃሚ ለመሆን ብዙ ያደጉ ሀገራት እየሰሩ መሆናቸውን ያነሱት አቶ አህደር እኛም ያለንን ጸጋ ለመጠቀም ዘርፉ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et