ለቱሪዝም ኢንዱስትሪው ቴክኖሎጂን መጠቀም የሚያስችል ጥናት ቀረበ ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በ2017 ዓ.ም ካደረጋቸው ጥናትና ምርምሮች መካከል በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፉ ተወዳዳሪ መሆን የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን የሚያሳይ ጥናት ቀረበ፡፡ ጥናቱን ያቀረቡት የአቶ ዳዊት ኃ/ሚካኤል ሲሆኑ፤ በጥናቱ የተለዩት ቴክኖሎጂዎች አፕልኬሽን ከመስራት እስከ ቁሳዊ እቃዎች ምርት የዳሰሱ ናቸው፡፡በጥናቱ የተካተቱት ሀገራችን ከሏት እንደ ህዳሴ ግድብ እና ጣና ሀይቆች ላይ ተጨማሪ መስህብ የሚሆኑ የውሃ ላይ ሆቴሎች (floating hotel)፣ ጎብኚዎችን ከአካባቢው ማህረሰብ ጋር ለመግባባትየሚያስችል የቋንቋ መተርጎሚያ አፕልኬሽን፣ አንድ ጎብኝ ፓርክ ውስጥ ሲገባ መንገድ እንዳይጠፋው የሚረዳ ጂፒኤስ እና በተለይ ከውጭ የሚገባ ጉብኝዎች የሚጠቀሙበት ታጣፊ ወንበር ምርቱን በሀገር ውስጥ መስራት እንደሚቻል ከተገለጹት ዋናዋናዎችቹ ናቸው፡፡ በዚህ ጥናት ከ30 በላይ ቴክኖሎጂዎች ተለይተው የቀረቡ ሲሆን በቴክኖሎጂ ዘርፍ መሰማራት የሚፈልጉ ተቋማት እና ወጣቶች ተደራጅተው መስራት የሚችሉት መሆኑን አቶ ዳዊት ገልጸዋል፡፡
እነዚህ ቴክኖሎጂዎች ለመስራትና ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልገው ወጪ ጥናቱ መለየቱን እና ይህን ለማሳካት ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የጀመራቸውን ሥራዎች ከሌሎች ተቋማት ጋር በቅንጅት ውጤታማ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ጥናቱን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልእክት ኢንስቲትዩቱ ከጊዜ ወደጊዜ በዘርፉ ያለውን ክፍተት የሚለዩ የጥናት እና ምርምር ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸው አቶ ዳዊትም የሰሩት ጥናት እንደሀገር ልንጠቀመት የሚገባ በመሆኑ በቀጣይ ሌሎች ባለድርሻዎችም ሊሳተፉበት የሚችል ሰፋ ያለ መድረክ እናዘጋጃለን ብለዋል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et

Recent Comments