በተቋሙ የተከናወኑ ምርምሮችን መሰረት በማድረግ የስልጠና ጥራትን የሚያሻሽሉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለጸ፡፡ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በ2017 በጀት ዓመት ካደረጋቸው ተግባራዊ ምርምሮችን መሰረት በማድረግ በተለይ የቱሪዝም ዘርፉን ስልጠና ለማሻሻል የሚያስችሉ ተግባራትን በማከናወን ውጤት መገኘቱን የሥልጠናና ተቋማት አቅም ግንባታ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት ገልጸዋል፡፡

ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ካደረጋቸው የተግራዊ ምርምር መካከል የቱሪዝም ሰልጣኞች የስልጠና አቀባበል፣ የመግለጽ ችሎታቸውን እና ለስልጠናው ያላቸውን በጎ አመለካከት ለማሳደግ ተግባራዊ ምርምሩን መሰረት በማድረግ በዘርፉ የሚገኙ ሙያተኞች ተጋብዘው ስልጠናዎች መሰጠታቸውን እንዲሁም በአዲስ አበባና ዙሪያው የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን ሰልጣኞች እንዲገበኙ መደረጉን በተለይ በዘርፉ ያለውን እድሎች የሚያሳዩ የማነቃቂያ ስልጠናዎች በኢንዱስትሪው ሙያተኞች ተሰጥቷል ብለዋል፡፡
ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ በቀጣይ ሥልጠና ዓመት በተለይ ለቱሪዝም ዘርፉ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ የገለጹት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በፋካልቲ ደረጃ እንዲቋቋም መደረጉና በሁለት ዲፓርትመንት መደራጀቱ የምርምር ውጤቶቹን ተግባራዊ ለማድረግ እና የዘርፉን ሰልጣኝ ቁጥር ለመጨመር ይረዳል ብለዋል፡፡
ልምድን መሰረት ያደረገ የአሰለጣጠን ዜዴ የአስጎብኝነት ክህሎትን ለማሳደግ ያለውን ተግባራዊ ምርምር ያቀረቡት የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ ተማራማሪ ዓለምነህ መርሻ ምርምሩ በተግባር የተሞከረ እና ትክክለኛ የአሰለጣጠን ዘዴን ያሳየ ምርምር መሆኑን ገልጸው ተቋሙ በቀጣይነት ተግባራዊ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል፡፡ በምርምሩ ግኝት መሰረት የተሞከሩ የአሰለጣጠን ዘዴዎች የሰልጣኞችን የማስጎብኘት ክህሎት የሚያሳድግ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et