ከ500 በላይ ሰልጣኞች በኢንዱስትሪዎች ለተግባር ስልጠና ተሰማሩ

August 21, 2026
ከ500 በላይ ሰልጣኞች በኢንዱስትሪዎች  ለተግባር ስልጠና ተሰማሩ

ቱ ማ ኢ
ነሐሴ 14/2018 ዓ ም
የፌደራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ የሚያሰልጠናቸውን 592 ሰልጣኞች ከ100 በላይ በሚሆኑ ሆቴሎችና የቱሪዝም ድርጅቶች ውስጥ በመመደብ የተግባር (Cooperative Training) ስልጠና መስጠት መጀመሩን ገለጸ።
በትብብር ስልጠናው ወቅትም የኢንስቲትዩቱ አሰልጣኞችና የዲፓርትመንት ኃላፊዎች ሰልጣኞች በተመደቡባቸው ተቋማት በአካል በመገኘት የሥራ አፈጻጸማቸውንና የሥራ ሥነ-ምግባራቸውን በቅርበት የመከታተልና የመገምገም ሥራ ማካሄዳቸው ተጠቅሷል።
የኢንስቲትዩቱ የትብብር ስልጠና ክፍል አስተባባሪ አቶ ሳለአምላክ እንደገለጹት፤ ስልጠናው ሰልጣኞች በክፍል ውስጥ የቀሰሙትን የንድፈ-ሐሳብ (Theory) እውቀት በቀጥታ ከኢንዱስትሪው ጋር በማገናኘት የሙያ ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ የታለመ ነው።
በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ በተግባር ስልጠና ላይ የሚገኙ ሰልጣኞች በበኩላቸው፤ በኢንዱስትሪው ውስጥ ገብተው መሳተፋቸው የተሻለ የሥራ ልምድ እንዲያካብቱና ለሥራው ዓለም ዝግጁ እንዲሆኑ ትልቅ ዕድል እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።
ኢንስቲትዩቱ ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ትስስር በማጠናከር የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ታውቋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less