በአምስት ዓመታት የለውጥ ጉዞ የተመዘገቡ ስኬቶችን የሚያበስር ኤግዚቢሽን እና የምክክር ጉባኤ ተዘጋጀ ነሐሴ 25/2018 ዓ ም

September 01, 2026
በአምስት ዓመታት የለውጥ ጉዞ የተመዘገቡ ስኬቶችን የሚያበስር ኤግዚቢሽን እና የምክክር ጉባኤ ተዘጋጀ ነሐሴ 25/2018 ዓ ም

ቱ ማ ኢ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ፣ ተጠሪ ተቋማቱ እና የክልል ቢሮዎች የተሳተፉበት ባለፉት አምስት ዓመታት ተቋማቱ ያከናወኗቸውን አበይት ተግባራትንና የተመዘገቡ ስኬቶችን የሚያሳይ አጠቃላይ ኤግዚቢሽን እና የምክክር ጉባኤ ተዘጋጅቷል፡፡
ይህ ኤግዚቢሽን እና የምክክር ጉባኤ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ብቁ፣ ተወዳዳሪና በክህሎት የበለፀገ የሰው ኃይል በማፍራት ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት አስተዋፅኦ ለማበርከት የያዘውን ተልዕኮ በተግባር ማረጋገጡን ያሳየ ነው ሲሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል ገልጸዋል፡፡።
በተጨማሪም በገለጻቸው በኢትዮጵያ የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማስፋፋት፣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትን ለማዘመን እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ባለሙያዎችን ለማፍራት የተቀመጠውን ራዕይ ስኬታማነት አመልክቷል ብለዋል።
ኢንስቲትዩቱ በተለይም በቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ዘርፍ ብቃት ያለው የሰው ኃይል በማሰልጠን ረገድ የነበረውን የላቀ ሚና ያበሰረ ሲሆን፣ ተቋማቱ ለወደፊት የተሻለ የሥራ ዕድል ለማስገኘትና በክህሎት ላይ የተመሠረተ ትውልድ ለመገንባት እና ዘርፉን በጥናትና ምርምር እየደገፉ ተልዕኮ ከመወጣት በላቀ ሁኔታ ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳየ ነው ተብሏል፡፡
የምክክር ጉባኤው ለቀጣይ አራት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less