ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በሀገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውን የኩሉነሪ አርትና የኢቨንት ማኔጅመት በደረጃ ስድስት/ዲግሪ ስልጠና መስጠት የሚያስችል ስርዓተ ትምህርት አዘጋጅቶ በባለድርሻ አካላት ተገምግሟል።
መድረኩን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ሲከፍቱ እንደተናገሩት በቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ዘርፍ ስልጠና በመስጠት አንጋፋ የሆነው ኢንስቲትዩቱ በዚሁ ዘርፍ ከመጀመሪያ ዲግሪ በደረጃ ስድስት እስከ ደረጃ ስምንት የፒኤችዲ አቻ ስልጠና ለመስጠት አቅዶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ እንደገለጹት በዚህ መድረክ ለውይይት የቀረቡት የኩሉነሪ አርትና ኢቨንት ማኔጅመንት ስርዓተ ትምህርት የተዘጋጀላቸው ሲሆኑ፤ የሆቴል ማኔጅመንት እና የቱሪዝም ማኔጅመንት ቀደም ሲል ስልጠናው በአፍሌሽን ከፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ጋር ሲሰራ የቆየ መሆኑን ነገር ግን ስርዓተ ትምህርቱ አዳዲስ ይዘቶችን ጨምሮ እንደገና መዘጋጀቱን ተናግረዋል።
ስርዓተ ትምህርቱን የኩሉነሪ አርቱን የሀዋሳ ዩንቨርሲቲ መምህር አቶ ደመቅሳ ሰንበታ የኢቨንት ማኔጅመንት ዶ/ር ኤፍፌም አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አቅርበው ግብዓት የሚሆኑ ሃሳቦች ከዘርፉ ባለሙያዎች ተሰጥቷል።
የሆቴል ማኔጅመንት እና ቱሪዝም ማኔጅመንት ስርዓተ ትምህርት ዝግጅትን ደግሞ ዶ/ር ካሰኝ ብርሃኑ ከደ/ብርሃን ዩንቨርሲቲ እና ዶ/ር ስንታየሁ ከመዳወላቡ ዩንሸርሲቲ ገምግመዋል ከተሳታፊዎችም ግብዓት የሚሆኑ ሃሳቦች ተሰባስቧል።
የዝግጅቱ ተሳታፊዎች የዚህ ስርዓተ ትምህርት ዝግጅት ተጠናቆ በ2018 ስልጠና እንዲጀምር ያላቸውን ጉጉት ገልጸው የረጅም ጊዜ ጥያቄያቸው መልስ ያገኘበት በመሆኑን የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et

Recent Comments