የዋና ዳይሬክተር መልዕክት

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በዘርፉ ፈጣን እድገት የሚያመጣ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የሰው ኃይል በማቅረብ ፤ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር፣ የማማከር እና የማሀበረሰብ አቀፍ አግልግሎት በመስጠት ለቱሪዝም ኢንዱስትሪው እድገት የበኩሉን አስተዋፆኦ እያደረገ የሚገኝ አንጋፋ መንግስታዊ ተቋም ነው ፡፡
ተቋማችን ላለፉት 55 ዓመታት በነበረው ሂደት የሀገራችን ቱሪዝም በስፋት ከሰዎች ልጆች ስልጣኔ እና ሉዋላዊነት ጋር ተያይዞ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዘርፉ የሰለጠነና የበቃ የሰው ኃይል ከማቅረብ አንፃር ያለብንን ውስንነቶች በማሻሻል በቴክኖሎጂና በዘመናዊ መሳሪያዎች የዳበረ ስልጠና መስጠት ይጠበቅብናል፡፡
በተጨማሪም ሀገራችን ያላትን የወጣት ኃይል በመጠቀም ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ መስህቦቻችንን በመጠበቅና በመንከባከብ ለዓለም በማስተዋወቅ በአፍሪካ ተወዳዳሪ የሆነ፣ ለኢኮኖሚያችንም ተገቢውን ድርሻ ማበርከት የሚችል ጠንካራ ተቋም ለመገንባት ጥረት ማድረግ የሁላችንም ኃላፊነት ነው፡፡
ስለሆነም የዘርፉን እድገት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት የተቋሙ ራተኞችና መምህራን ከፍተኛ ኃላፊነት ያለባቸው በመሆኑ ያለንን ውስን ሀብት በመጠቀም የተጣለብንን ኃላፊነት እንድናወጣና የሀገራችንን ቀደምት የስልጣኔ ታሪክ አሻራን በማስቀጠል ኢትዮጽያን ተመራጭና ተወዳዳሪ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ በጋራ እንስራ የሚል መልዕክቴን አስተላልፋለሁ፡፡