በልምድ የተገኘን እውቀት እውቅና መስጠት ቱ ማ ኢ መስከረም 5/2019 ዓ.ም |
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከፐብሊክ ሲርቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ለመጡ ባለሙያዎች የተግባር ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡
ኢንስቲትዩት በልምድ ያበረከቱትን እውቀትና ክህሎት እውቅና ለመስጠትና ይበልጥ ለማበልፀግ ያለመ የተግባር ስልጠና እየተሰጠ ነው ።
ይህ የስልጠና ፕሮግራም ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ለተውጣጡ 180 ባለሙያዎች የሚሰጥ ሲሆን፤ ትኩረቱንም በሚከተሉት ዋና ዋና ዘርፎች ላይ አድርጓል፡፡
በምግብ ዝግጅት (Culinary Arts) ፣ በምግብና መጠጥ መስተንግዶ (Food & Beverage Service) እና በእንግዳ አቀባበል (Front Office/Hospitality)
ስልጠናው በኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ ልምድና እውቀት ባላቸው አሰልጣኞች የሚሰጥ ሲሆን፤ ሰልጣኞቹ በልምድ ያካበቱትን የተግባር ልምድ በዘመናዊ የሙያ መስፈርት ለማደራጀትና አገልግሎታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ትልቅ አቅም ይፈጥርላቸዋል።
ኢንስቲትዩታችን የቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ዘርፉን የሰው ሃይል አቅም ለማሳደግና የሥራ ላይ ልምድን በሙያዊ እውቅና ለመደገፍ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል!
እርስዎም ይምጡ ያለዎትን ልምድ በስልጠና ያሳድጉ፤ በብቃት ማረጋገጫ የሙያ ህይወትዎን ይለውጡ!»
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less