ቱ ማ ኢ ጥር/23/2018 ዓ ም ለቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አሰልጣኞችና ባለሙያዎች የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ፖሊሲ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
ሰነዱን ያቀረቡት በሥራና ክህሎት ሚንስቴር የሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ ዶ/ር ተሾመ ለማ ናቸው።
የቴክኒክና ሙያ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ የሚሸከም ባለሙያ ማለትም በክህሎት የበለፀገ ሀገር ወዳድ ፣ሥራ ፈጠሪና ከፍተኛ ፈጠራ ችሎታን የተላበሰ የሰው ሀይልን የሚያፈራ ሆኖ ማየትን ዋና ዓላማ ተደርጎ የተሰራ መሆኑን ባቀረቡት ሰነድ አመላክተዋል።ዶ/ር ተሾመ በገለፃቸው በቴክኒክና ሙያ የቱሪዝም ሴክተሩ ከፍተኛ የሰው ኃይል ማምረት የሚያስችል ኢንደስትሪ መሆኑን እና በጥናት የተለየው ወደሥራ መግባት ያለበት የወጣት ቁጥር ደግሞ ከ70 በመቶ በላይ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ስለሆነም ኢንስቲትዩቱ በስልጠናና በጥናት ሰፊ ሥራዎች እንደሚያስፈልገው ተገልጿል።
ባጠቃላይ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችሎታን የተላበሰ የሰው ሀይልን የሚያፈራ ሆኖ ማየት የሚያስችል ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ወደሥራ መገባቱ ተገልጿል።
በቀረበው ሰነድ ዙሪያም ጥያቄና አስተያየት ተሰጥቷል።
ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et


Recent Comments