ቱ.ማ.ኢ ጥር 23/2018 ዓ.ም የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የሪፎርምና ISO 21001 2018 ያለበት የተግባር ምዕራፍ ግምገማ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ። በውይይቱ ሁሉም የሥራ ክፍሎች የሪፎርምና የISO 21001 2018 አተገባበር ቀጣይነትን ይዞ ከመሄድ አኳያ ያሉበት ደረጃ በሱፐርቪዥን ቡድን ተፈትሿል። ውጤትም ከፍተኛ፣መካከለኛ እና ዝቅተኛ የሚል ደረጃ የተሰጠ ሲሆን ከሱፐርቪዥን ቡድኑ ምልከታ በኋላ በርካታ ሥራዎች መሻሻል እንደታየባቸው ተገልጿል። የሱፐርቪዥን ሪፖርቱን የቡድኑ አስተባባሪ አቶ ሰለሞን አሰፋ አቅርበዋል።
ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et


Recent Comments