ቱ.ማ .ኢ ጥር 23/2018 ዓ ም በዚህ ፕሮግራም የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለጹት ጥራት ያለው ስልጠና ምርምርና ማማከር የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖር የተሰሩ ሥራዎችን እየገመገምን ሁሉም የተሰጠውን ተልዕኮ መወጣቱን ለማየት ነው ብለዋል።አቶ ጌታቸው አክለውም የጋራ የሚያደርጉንን ምርኩዞች በመያዝና ቀጣይ ለምንሰራቸው ሥራዎች ዝግጁ የምንሆንበት የተለያዩ ስልጠናዎች እንደሚኖሩ ገልጸው በዚህ የምክክር መድረክ ሠራተኞች በብቃት እንዲሳተፉ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

የተቋሙ ስትራቴጂክ ጉዳዩች ሥራ አስፈጻሚ በአቶ ዳግም አዲሱ የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ሪፖርት ለሠራተኞች አቅርቧል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et