ቱ ማ ኢ ጥር 15/2018 ዓ ምበቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከዓለም ባንክ ድጋፍ EASTIRP ፕሮጀክት ግዥ ሥርዓቱ ወደ ኤሌክትሮኒክስ በመቀየሩ ሥራው ለሚመለከታቸው ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ነው።ስልጠናውን የከፈቱት የተቋሙ የሥራ አመራርና አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ እንደገለፁት ከዚህ በፊት የነበረውን የግዥ ሥራ ጫና የሚቀንስና የጊዜና ጉልበት ቆጣቢ የሆነውን ሲስተም ሥራው የሚመለከታቸው ባለሙያዎች እና የEASTIRP ፕሮጀክት ባለሙያዎች ይህንን ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመውሰድ የግዢ ሥራው ቀልጣፋ እንዲሆን ያስችላል ብለዋል።

በመቀጠልም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ሁሉም በትኩረት በመከታተል የተገኘውን እድል መጠቀም መቻል እንዳለበት አሳስበዋል።
ስልጠናው የሚያካትተው ስለ EGP ምንነት፣ ጠቀሜታው እና ቀጣይ አሰራሮችን እንደሆነ የጠቆሙት ከፌዴራል ግዥና ፋይናንስ ከፍተኛ ባለሙያዎች አቶ ዋለልኝ አሰፋ እና አቶ ሀብተወልድ ተሾመ ናቸው።
አራቱን የግዥ አይነቶች አቅርቦት፣ ግንባታ ፣ አገልግሎት እና ማማከር ወረቀት አልባ በሆነ መንገድ እንዴት መስራት እንደሚቻል ግንዛቤ ተሰጥቷል።
በተቋማችን ላለፉት ሦስት ዓመታት በወርልድ ድጋፍ የEASTIRP ፕሮጀክት ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል።
​ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et