ኢንስቲትዩቱ በሆቴልና ቱሪዝም ሙያዎች በደረጃና በዲግሪ ያሰለጠናቸውን አስመረቀ ቱ.ማ.ኢ ሐምሌ 13/2017 ዓ.ም

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በሆቴልና ቱሪዝም ሙያዎች በዲግሪና በደረጃ ያሰለጠናቸውን 481 ሰልጣኞች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት አስመርቋል።

Read More

ቱ.ማ.ኢ ሰኔ 26/2017 ዓ.ም

በተቋሙ የተከናወኑ ምርምሮችን መሰረት በማድረግ የስልጠና ጥራትን የሚያሻሽሉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለጸ፡፡ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በ2017 በጀት ዓመት ካደረጋቸው ተግባራዊ ምርምሮችን መሰረት በማድረግ በተለይ የቱሪዝም ዘርፉን ስልጠና ለማሻሻል የሚያስችሉ ተግባራትን በማከናወን ውጤት መገኘቱን የሥልጠናና ተቋማት አቅም ግንባታ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት ገልጸዋል፡፡

Read More

ሰኔ 21/2017 ዓ.ም

ኢንስቲትዩቱ በኢስትሪፕ ፕሮጀክት የተከናወኑ ሥራዎች ሪፖርት ለአማካሪ ቦርዱ አቀረበ።ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በ2017 በጀት ዓመት በኢስትሪፕ(EASTIP) ፕሮጀክት የተከናወኑ ሥራዎች ሪፖርት እና የቀጣይ በጀት ዓመት እቅድ ለአማካሪ ቦርዱ አቀረበ ።የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ በፕሮግራሙ መክፈቻ እንደተናገሩት አማካሪ ቦርዱ በጥናትና ምርምር፣ በትብብር ስልጠና ፣ በሥርዓተ ትምህርት ዝግጅት እገዛው ላቅ ያለመሆኑን እንስተዋል፤ ምስጋናም አቅርበዋል።

Read More

ቱ.ማ.ኢ ሰኔ 20/ 2017 ዓ.ም

ለቱሪዝም ኢንዱስትሪው ቴክኖሎጂን መጠቀም የሚያስችል ጥናት ቀረበ ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በ2017 ዓ.ም ካደረጋቸው ጥናትና ምርምሮች መካከል በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፉ ተወዳዳሪ መሆን የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን የሚያሳይ ጥናት ቀረበ፡፡ ጥናቱን ያቀረቡት የአቶ ዳዊት ኃ/ሚካኤል ሲሆኑ፤ በጥናቱ የተለዩት ቴክኖሎጂዎች አፕልኬሽን ከመስራት እስከ ቁሳዊ እቃዎች ምርት የዳሰሱ ናቸው፡፡በጥናቱ የተካተቱት ሀገራችን ከሏት እንደ ህዳሴ ግድብ እና ጣና ሀይቆች ላይ ተጨማሪ መስህብ…

Read More

ቱ.ማ.ኢ ሰኔ 19/2017 ዓ.ም

የባህል ምግቦች ለሥራ ዕድል ፈጠራ የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ በስልጠና መደገፍ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በ2017 ዓ.ም ካደረጋቸው ጥናትና ምርምሮች መካከል የባህል ምግቦችን ለሥራ እድልና ለኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የሚያሳይ ጥናት ቀረበ፡፡ ጥናቱን ያቀረቡት አቶ አህደር ጠና በአስር የክልል ከተሞች ላይ በተደረገ ጥናት ከ14 ሺህ በላይ ሰዎች በባህል ምግብ ዝግጅት ሥራ ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

Read More

ቱ.ማ.ኢ ሰኔ 17/2017 ዓ.ም

የሀገራችንን ቱሪዝም ዘላቂነት ለማረጋገጥ የኢትዮጵያ ሆስፕታሊቲ አገልግሎት ደረጃ ሊኖር እንደሚገባ ተገለጸ ።የቱሪዝም ዘርፉን እንቅስቃሴ ዘላቂነት በማረጋገጥ ከዘርፉ ተጠቃሚ ለመሆን በሁሉም ሆቴሎችና የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ተቀራራቢ አገልግሎት ለመስጠት ሀገር አቀፍ የሆስፕታሊቲ አገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ ሊኖር እንደሚገባ የኢንስቲትዩቱ የጥናት ምርምርና ማማከር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ሥዩም ገለጹ ።

Read More

የሆቴል አገልግሎት የደምበኞችን ፍላጎት የተከተለ መሆን እንደሚገባው ተገለጸ ።

ቱ.ማ.ኢ ሰኔ 17/2017 ዓ.ም ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከሊድዋይስ ድርጅት ጋር በመሆን ዘመኑ የደረሰበትን የሆቴል አገልግሎት ለመስጠት የሰው ሀብት ተሰጥኦ ማስተዳደር ላይ ለሆቴል ሥራ አስኪያጆችና ሰው ሀብት ኃላፊዎች ስልጠና ተሰጥቷል ።የስልጠና መርሐ ግብሩን ያስጀመሩት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ማሰልጠኛ ተቋሙ በዘርፉ ውስጥ የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ የሰለጠነ የሰው ሀይል እያቀረበ ነው፣ በዘርፉ ላይ ችግር ፈቺ…

Read More

ቱ.ማ.ኢ ሰኔ 17/2017 ዓ.ም

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከደብረብርሃን ዩንቨርሲቲ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከደብረብርሃን ብርሃን ዩንቨርሲቲ ጋር በቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ዘርፍ በአሰልጣኞች አቅም ግንባታ፣ በትብብር ስልጠና እና በጥናትና ምርምር ዘርፎች እንዲሁም በትብብር ስልጠና አብሮ ሊሰሩ በሚያስችላቸው ጉዳዮች ዙሪያ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

Read More

ቱ.ማ.ኢ ሰኔ 16/2017 ዓ.ም

ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ በ2017 ባከናወናቸው ጥናትና ምርምሮች ላይ ውይይት ተካሄደ ።ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በበጀት ዓመቱ በቱሪዝም እሴት ሰንሰለት፣ የሆስፕታሊቲ ዘርፉ አስፈላጊ ቴክኖሎጂዎች፣ የባህል ምግቦች ዝግጅት ሀገር በቀል እውቀቶችና ሌሎችም ርዕሶች ላይ ባካሄደው ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮች ላይ ውይይት ተካሄደ ።በጥናት ጉባኤው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ በበጀት ዓመቱ በተቋሙ የተሰሩ ጥናቶች…

Read More

ሰኔ 15/2017 ዓ ም

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በቱሪዝምና ሆቴል ዘርፍ ለሰልጣኞች የትብብር ስልጠና ለሚሰጡ ባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ። በመክፈቻ ፕሮግራሙ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ የስልጠና እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት ተቋሙ በሆቴልና ቱሪዝም ሙያ ዘርፍ በስልጠና፣ በምርምርና ማማከር እንዲሁም በቴክኖሎጂ ሽግግር ግንባር ቀደም ሆኖ መቀጠል የቻለው ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እና በቅንጅት…

Read More