ለአዲስ ስልጠና ፈላጊዎች በሙሉ!!
ለአዲስ ስልጠና ፈላጊዎች በሙሉ!!
ምዝገባ ከምስከረም 11/2019 ዓ.ም ጀምሮ ባሉ ተከታታይ ሁለት ሳምንታት ዘወትር በሥራ ሰዓት
ከፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የተላለፈ
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩትም በአዲሱ ዓመት የሙያ ጉዞዎን የሚያደምቁና ለስኬት የሚያበቁ የስልጠና እድሎችን ይዞልዎት ቀርቧል!
ተቋማችን ከ1961 ዓ.ም ጀምሮ (ላለፉት 57 ዓመታት) በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ብቁ ባለሙያዎችን በማፍራት፣ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር በማካሄድ እንዲሁም ዘመናዊ የማማከርና የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት በመስጠት የሚታወቅ አንጋፋና መሪ ተቋም ነው።
🌟 ኢንስቲትዩታችንን ልዩ እና ተመራጭ የሚያደርገው
የተቋሙ ልዩ መለያዎች፦ ዝርዝር ማብራሪያ
ዓለም አቀፍ ጥራት፦ ISO 21001:2018 በትምህርት አስተዳደር ጥራት እውቅና ያገኘ
የላቀ እውቅና፦ በግራንድ አፍሪካን የተቋማትና የአመራር ሽልማት የዳይመንድ ደረጃ ተሸላሚ
ተግባር ተኮር ስልጠና፦ በዘመናዊ ወርክሾፖችና ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ባላቸው የሆቴል ሶፍትዌሮች የተደገፈ
የቋንቋ ክህሎት፦ የተግባቦት አቅምን ለማሳደግ በእንግሊዘኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ጀርመንኛ እና አረቢኛ ይሰጣል
የስልጠና መርሃ ግብር በቀን መደበኛ፣ በማታ፣ በእረፍት ቀናት (ቅዳሜና እሁድ) እንዲሁም በአጫጭር ስልጠናዎች
🎓 የሚሰጡ የትምህርትና የስልጠና ፕሮግራሞች
1. የደረጃ (Level III & IV) እና የደረጃ 5 (Level V) ስልጠናዎች
• Front Office Service (በእንግዳ አቀባበል)
• Housekeeping and Laundry Service (በቤት አያያዝ)
• Food and Beverage Control (በምግብና መጠጥ ቁጥጥር)
• Food and Beverage Service (በምግብና መጠጥ መስተንግዶ)
• Tour Guide (በቱሪስት አስጎብኚነት)
• Pastry and Bakery Production (በኬክና ዳቦ አሰራር)
• Culinary Art (በምግብ ዝግጅት ጥበብ - Level IV & V)
• Tour Operation (በቱር ኦፕሬሽን - Level V)
2. በዲግሪ (Degree Program)
• Hotel Management (የሆቴል ማኔጅመንት)
• Tourism Management (የቱሪዝም ማኔጅመንት)
• Event Management (የኢቨንት ማኔጅመንት)
• Culinary Art (የኩሊናሪ አርት / የምግብ ዝግጅት ጥበብ)
📍 አድራሻ
• አድራሻ: አዲስ አበባ፣ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ (ገነት ሆቴል)
• ስልክ ቁጥር: +251 99 401 1793 / 011 530 1811 / 011 530 8106
• ፖስታ ሣጥን ቁጥር: 4350
• ኢሜይል: infotti.edu.et
• Facebook: tticommunication
• Telegram: tticommunication
• TikTok: @ftti_official
በአዲሱ ዓመት እንደ አደይ አበባ ፈክተው በሙያዎ የላቀ ደረጃ ላይ ይድረሱ! ይምጡ፣ ይሰልጥኑ፤ እኛ ብቁ ባለሙያ እናደርግዎታለን!
ለላቀ ብቃት እንተጋለን!
ለምዝገባ ሲመጡ
• የ8ኛ ክፍል ካርድ
• ትራንስክሪፕት
• 2 ጉርድ ፎቶ ግራፍ
• የፋይዳ መታዎቂያ፤ ያስፈልጋል See less