ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በ20ኛው ግራንድ አፍሪካ የአመራርና የተቋማት ሽልማት ተሸላሚ ሆነ። ግራንድ የአፍሪካ የተቋማት እና የአመራር ሽልማት ድርጅት፣ በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የልማት መስኮች የላቀ አፈፃፀም ላሳዩ ተቋማትና አመራሮች እውቅና በሚሰጥበት 20ኛው የሽልማት መርሃ-ግብር ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ቱሪዝም ዘርፍ ላለፉት 57ዓመታት ለነበረው አበርክቶ ድርጅቱ የራሱን ባለሙያዎች ልኮ አስጠንቶ እንዲሁም ባወጣው ጥብቅ መስፈርት መሠረት ተመዝን የዳይመንድ ደረጃ ተሸላሚ ሆኗል፤ትጉሆችንምአመስግኗል።ሽልማቱተቋማትና አመራሮች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ተቀባይነት እንዲኖራቸው ማድረግ፣ጥራት ያለው ምርትና አገልግሎት እንዲቀርብ ማበረታታት ዓላማ ያደረገ የእውቅና መርሀ ግብር መሆኑ ተገልጿል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ ፌስቡክ፡
https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et


Recent Comments