ፌ.ቱ.ማ.ኢ ጥር 14/2018 ዓ ምየፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ሠራተኞች የአብሮነት ቀንን በጉለሌ እፀዋት ማዕከል በጉብኝትና በሌሎች ፕሮግራሞች እያከበሩ ነው።
በፕሮግራሙ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደተናገሩት የሠራተኞች አብሮነት ቀንን ማክበር እንደተቋም፣ እንደ ሀገር ያሉንን የጋራ እሴቶች ለማጠናከር እድል ይፈጥርልናል ብለዋል።አቶ ጌታቸው አያይዘውም በአዲስ አበባ የሚገኘው የእጸዋት ማዕከል የኢኮ ቱሪዝም መዳረሻ በመሆኑ ለሠራተኛው በቂ ግንዛቤ እንዲኖረውና ለስልጠና፣ ለጥናትና ምርምር እንዲሁም የማማከር አገልግሎት በጋራ ለመስራት እድል ይፈጥርናል ብለዋል።
ሠራተኞች በማዕከሉ የእግር ጉዞ በማድረግ አካባቢውን ጎብኝተዋል።
በተጨማሪም የላቀ የደንበኞች አገልግሎት ስልጠና የወሰዱ የተቋሙ ሠራተኞች የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et


Recent Comments