#ጋዜጣ_ፕላስ | የቱሪዝም ማስልጠኛ ኢንስቲትዩት በትላልቅ ሆቴሎች በምግብ ሜኑነት
እንዲካተቱ በጥናት ለይቶ ያቀረባቸው 31 የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች የተሳተፉበት የባህላዊ የምግብ ፌስቲቫል እያካሄደ ይገኛል።የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል እንደገለጹት፤ ሚኒስትሩ የስራ እድል ለመፍጠር የቤት ስራ የወሰደ ተቋም እንደመሆኑ በቱሪዝም ዘርፉ ተፈላጊነት ያላቸዉን ባለሙያዎች እያሰለጠነ ይገኛል።
ፌስቲቫሉም የኢትዮጵያን መልክ ከማስተዋወቅ በተጨማሪ ባህላዊ ምግቦች ሀብት የሚፈጠርባቸዉ እንዲሆኑ፣ እናቶችና ወጣቶች አዳዲስ የስራ እድል እንዲፈጥሩ የሚያነሳሳ መሆኑ ገልጸዋል።
የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጌታቸዉ ነጋሽ በበኩላቸዉ፤ የቱሪዝሙ ዘርፍ ከማህበራዊ ዘርፍ ወደ ኢኮኖሚ ዘርፍ የተሸጋገረ በመሆኑ በተለያየ መልኩ ያሉ የቱሪዝም ሀብቶችን ለማዉጣት እየተሰራ ይገኛል።
ከቱሪዝም ሀብቶች አንዱ የምግብ ዘርፉ በመሆኑም ባህላዊ ምግቦች እንዲተዋወቁና በትላልቅ ሆቴሎች እንዲካተቱ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል።
በዚህም የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች ባህላዊ ምግቦች በትላልቅ ሆቴሎች ሜኑ ውስጥ ማካተት መቻሉን ጠቅሰዋል።
መስከረም ሰይፉ
++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ #gazette_plus

Recent Comments