ራዕዩን ለማሳካት ሠራተኞችን ማብቃት

October 05, 2026
ራዕዩን ለማሳካት ሠራተኞችን ማብቃት

መስከረም 16/2019 ዓ ም
ቱ .ማ. ኢ
የፌደራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የተጣለበትን ሀገራዊ ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት እና የላቀ የአገልግሎት አሰጣጥ ባህልን ለመገንባት ያለመ በዲጂታል እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለአስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞቹ ሰጠ።
«ራስን መግዛት እና ለደንበኛ ቅድሚያ መስጠት » በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው በዚህ ስልጠና ላይ በዘርፉ ሰፊ ልምድ ያላቸው የማህበራዊ ልማትና አመራር ሳይንስ ተመራማሪው አቶ ዘላለም ይትባረክ አነቃቂና አስተማሪ ትምህርቶችን አቅርበዋል።
አቶ ዘላለም በመልእክታቸው፦ “ማንኛውም ተቋማዊ ስኬት የሚጀመረው ከግለሰብ አስተሳሰብ ለውጥ ነው። እራስን ማሸነፍ ማለት ውስጣዊ ፍላጎትን፣ የሥራ ተነሳሽነትን እና ስነ-ምግባርን በመግራት ለተቋሙ ራዕይ መሳካት በቁርጠኝነት መቆም ነው” ብለዋል።
በሌላም በኩል ዘመኑን የሚመጥን እንዲሁም የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ግብ ለማሳካት የኢንስቲትዩቱ ሠራተኞች ራሳቸውን በእውቀት መገንባት የሚያስችል ዲጂታል እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በሚል በአቶ ፈቃዱ ቀነኒሳ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ስፔሻሊስት ስልጠና ተሰጥቷል።
አቶ ፍቃዱ እንዳሉት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥራን ማቅለል ለተለያዩ ችግሮች መፍትሔ የሚሰጥ መሆኑን፤ ብዙዎች ሥራችንን ይወስዳል ብለው እንደሚሰጉ ነገር ግን ጊዜንና ሀብትን በእጅጉ እንደሚቆጥብ ፣ድካምን እንደሚቀንስ አስረድተዋል።
የኢንስቲትዩቱ አስተዳደር ዘርፍ ሠራተኞችም በበኩላቸው የስልጠናው መዘጋጀት በስራቸው ላይ ተነሳሽነትና ጉልበት እንደፈጠረላቸው ገልጸው፤ የተቋሙን ራዕይና ተልዕኮ እውን ለማድረግ ባለሙሉ ፍላጎትና በቅንነት አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
ተቋሙ በቀጣይ የሰራተኞቹን አቅም በማሳደግ በቱሪዝም ዘርፉ የላቀ የሰለጠነ የሰው ሀይል ለማፍራት የሚደርገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less