የአመለካከት ለውጥና የሥራ ተነሳሽነትን የሚያጎለብት ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
ቱ ማ ኢ
መስከረም 14/2019 ዓ.ም
የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ለአስተዳደር ዘርፍ ባለሙያዎች የአመለካከት ለውጥ ማምጣት ለሚቀጥለው የሥራ ህይወት ስላለው ጠቀሜታ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
በስልጠናው መድረክ ላይ የተገኙት የተቋሙ ሥራ አመራር እና አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ ሥራን አክብሮ በመስራትና በህብረት በመንቀሳቀስ ዙሪያ ጠንካራና ጠቃሚ የሥራ መልዕክት አስተላፍለዋል።
የስልጠናው አዘጋጅና አስተባባሪ የሆኑት የ EASTRP ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ አብርሃም ለገሠ በበኩላቸው፤ ስልጠናው ሠራተኞች ለሥራቸው ከፍተኛ ተነሳሽነት እንዲኖራቸውና የሚመጡ የልማት ለውጦችን በአዎንታዊ መልኩ እንዲገነዘቡ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸው፣ ሰልጣኞች በትጋት እንዲከታተሉ አሳስበዋል።
ስልጠናውን በዋናነት የመሩት የማህበራዊ ልማትና አመራር ሳይንስ ተመራማሪው አቶ ዘላለም ይትባረክ ሲሆኑ፤ በመልካም ስነ-ምግባርና ባህሪ ለመቀጠል ሥራን ማክበር፣ ምስጋና፣ ደግነት፣ ይቅርታ እና ጠንካራ ህብረት ወሳኝ መሆናቸውን አሳታፊ በሆነ መልኩ ግንዛቤ በሚሰጥ መልኩ ስልጠናው ተሰጥቷል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less