ኢንስቲትዩቱ ሲሰጥ የነበረውን የአሰልጣኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና አጠናቀቀ።
መስከረም 22/2019 ዓ ም
የፌደራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ለአሰልጣኞቹ በተለያዩ የሙያና ክህሎት ርዕሶች ላይ ሲሰጥ የቆየውን የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የአቅም ግንባታ ስልጠና በስኬት አጠናቋል።
የስልጠናው የማጠቃለያ መርሃ-ግብር አካል የሆነው Project Beside ስልጠና መነሻነት፣ ሁሉም የስልጠና ክፍሎች (ዲፓርትመንቶች) የሰለጠኑበትን እውቀት ወደ ተግባር የለወጡባቸውን አጫጭር ፕሮጀክቶች አዘጋጅተው አቅርበዋል።
በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የሶፍት ስኪል (Soft Skills) ክፍል አስተባባሪ እታፈራሁ ሲሳይ ለአሰልጣኞች በተለይም የምዘና አዘገጃጀት እና የውጤት አሰጣጥ ስርዓት ላይ ያተኮረ ሰፊ ግንዛቤ ሰጥተዋል።
አሰልጣኞች የሰልጣኞችን ብቃት በትክክል ለመመዘን የሚያስችሏቸውን ዘመናዊ ዘዴዎችና መስፈርቶች በተግባር የተደገፈ ማብራሪያ አግኝተዋል።
በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ የስልጠና እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት እንደገለጹት መሰል የአቅም ማጎልበቻ መርሃ-ግብሮች የኢንስቲትዩቱን የስልጠና ጥራት ለማሳደግ እና አሰልጣኞች በዘመናዊ አሰራር እንዲታጠቁ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል።
አክለውም በተዘጋጁት ፕሮጀክቶችና በተቀሰሙት እውቀቶች አማካኝነት በተግባር የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ አቅጣጫ አስቀምጠው ስልጠናው ተጠናቋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less