የቱሪዝም ዘርፉን የላቀ የሰው ኃይል ፍላጎት ለማሟላት የተዘጋጀ ልዩ ስልጠና
መስከረም 21/1/2019 ዓ.ም
ቱ.ማ.ኢ
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና በክህሎት የበለፀገ የሰው ኃይል የማፍራት ተልዕኮውንና ራዕዩን እውን ለማድረግ፣ ለአሰልጣኞቹ የስልጠና አሰጣጥ ሂደቱን ለማዘመን የሚያስችሉ አጫጭር የሙያ ማሻሻያ ስልጠናዎችን ሰጥቷል።
በስልጠናው ላይ የተገኙት የተቋሙ የስልጠና እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት ባስተላለፉት መልዕክት፡ መሰል ስልጠናዎችን በህብረትና በቅንጅት መውሰድ ለአዲሱ የስልጠና ዘመን ስኬት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸው፣ አሰልጣኞች የተገኘውን እውቀት በብቃትና በትጋት በመተግበር የኢንስቲትዩቱን የስልጠና ጥራት ወደ ላቀ ደረጃ እንዲያሸጋግሩ አሳስበዋል።
በመድረኩ ከተሰጡት አበይት ስልጠናዎች መካከል በተቋሙ አሰልጣኝ በአቶ ዳንኤል በቀለ አማካኝነት ስለ "Planning Training Session"፣ ስለ ውጤት ተኮር የካሪኩለም ትግበራ (OB Curriculum) እና ስለ "Session Plan" አዘገጃጀት ሰፊ ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀርቧል። አሰልጣኞቹ የተሰጣቸውን ስልጠና መነሻ በማድረግ በየዲፓርትመንታቸው የራሳቸውን የትምህርት ክፍለ-ጊዜ ዕቅድ (Session Plan) አዘጋጅተው በተግባር ያቀረቡ ሲሆን፣ ሰፊ ውይይትም ተካሂዶበታል።
በዚህም መነሻነት ለሁሉም ዲፓርትመንቶች ወጥ የሆነና ሁሉም የተስማማበት የትምህርት ክፍለ-ጊዜ ዕቅድ ተዘጋጅቶ እንደሚቀርብ ተገልጿል።
በተጨማሪም Project Based Training ከፌደራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት የመጡት አቶ ትልቅሰው ለታ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጥተዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less