ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ነባር ሰልጣኞቹን ተቀበለ
መስከረም 25/2019 ዓ.ም
ቱ.ማ.ኢ
በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ለአንድ ዓመትና ከዚያ በላይ ስልጠናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው፣ ባለፉት ሁለት ወራት በኢንዱስትሪ የተግባር ስልጠና (Cooperative Training) ላይ የነበሩ ነባር ሰልጣኞች ለ2019 ትምህርት ዘመን ወደ ተቋሙ በመመለሳቸው አቀባበል ተደረገላቸው።
በመድረኩ የተገኙት የተቋሙ የስልጠናና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት ሰልጣኞቹ የተግባር ስልጠናቸውንና የረፍት ጊዜያቸውን በሰላም አጠናቀው በመመለሳቸው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አቶ ሀብታሙ አክለውም ሰልጣኞች እስካሁን ባገኙት እውቀት፣ ክህሎትና መልካም አመለካከት ምክንያት አንዳንዶቹ ገና ስልጠናቸውን ሳይጨርሱ ከሥራ እድል ጋር መገናኘት መጀመራቸውን ገልጸዋል። ሰልጣኞቹ በቀሪው የስልጠና ጊዜያቸው የተቋሙን ደንብና መመሪያ በመከተል፣ በሰዓት አክባሪነትና በትጋት ስልጠናቸውን እንዲከታተሉ አሳስበዋል።
በተመሳሳይ የተቋሙ የኳሊቲ አሹራንስ ክፍል አስተባባሪ ዶ/ር አስቻለው አደራ ሰልጣኞች በተቋሙ ቆይታቸው ሊከተሏቸው ስለሚገቡ መመሪያዎችና ሊያደርጓቸው ስለማይገቡ ህጎች ሰፊ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን፤ የቮኬሽናልና ጋይዳንስ ክፍል አስተባባሪ አቶ ታደሰ ሞላም ለሰልጣኞቹ መልካም የትምህርት ዘመን እንዲሆንላቸው በመመኘት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less