በደሴ ከተማ የተሰጠው የቱሪዝም ባለሙያዎች ስልጠና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ!

October 26, 2026
በደሴ ከተማ የተሰጠው የቱሪዝም ባለሙያዎች ስልጠና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ!

ቱ ማ ኢ
ጥቅምት 15/2019 ዓ.ም
የፌደራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከደሴ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ጋር በመተባበር ለ3 ቀናት ሲሰጥ የነበረው አጠቃላይ ስልጠና ተጠናቀቀ።
በዚህ ስልጠና ከ21 ከፍተኛ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት የተውጣጡ ቁጥራቸው 500 የሚሆኑ ባለሙያዎች በሆቴል ማናጅመንት፣ በምግብ ዝግጀት፣ በምግብና መጠጥ መስተንግዶ፣ እንግዳ አቀባበል እና በቤት አያያዝ ዘርፎች ተሳትፈዋል።
ስልጠናው የተግባር እና የንድፈ ሃሳብ በመሆኑ ሠራተኞች በቀላሉ በስራ ላይ ሊተገብሯቸው የሚችሏቸውን ክህሎቶች ጨብጠዋል፤
የአገልግሎት ጥራትና ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን በማካተት የቱሪስቶች የቆይታ ጊዜ የሚያራዝም አሰራርን አስተዋውቋል፤
በማጠቃለያ ፕሮግራም የተገኙት የደሴ ከተማ ባህል ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሰይድ አራጋው ስለስልጠናው ውጤታማ የተግባቦት ክህሎትና የደንበኛ ተኮር አሰራርን በማስፈን የደንበኞች እና የጎብኚዎችን እርካታ ያረጋግጣል፣ የምግብ ዝግጅት እና የቤት አያያዝ ጥራትን ከፍ ያደርጋል፤
የደሴን ከተማና የሀገር ገጽታ በመገንባት ለኢኮኖሚ ዕድገት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል።
የኢንስቲትዩቱ የማታ እና አጫጭር ትምህርት ክፍል ዲን አቶ ዳንኤል በቀለ በስልጠናው ለተባበሩ ሆቴሎች እና ለተሳታፊዎች ሁሉ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፣ መሰል አበረታች ስልጠናዎች በቀጣይም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less