ኢንስቲትዩቱ ከሀዋሳ ዩንቨርሲቲ ጋር የልምድ ልውውጥ አካሄደ ።

October 16, 2026
ኢንስቲትዩቱ  ከሀዋሳ ዩንቨርሲቲ ጋር የልምድ ልውውጥ አካሄደ ።

ቱ ማ ኢ
ጥቅምት 5/2019 ዓ.ም
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የጥናትና ምርምር ዘዴን፣ ክህሎትንና ጥራትን ለማሳደግ ያለመ የልምድ ልውውጥና የስልጠና መርሃ-ግብር አካሄደ።
ይህ ዓይነቱ ስልጠና በተቋማት መካከል የሚደረግ የጋራ ትብብር በተለይም በቱሪዝምና እንግዳ ተቀባይነት (Tourism & Hospitality) ዘርፍ የሚደረጉ ምርምሮች በተግባር ላይ የተመሰረቱና የዘርፉን ችግሮች የሚፈቱ እንዲሆኑ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሏል።
ስልጠናውን የዩንቨርሲቲው የጥናትና ምርምር ክፍል ያስተባበረው ሲሆን ተባባሪ ፕሮፌሰር ኦብሳ ተፈሪ ስልጠናውን ሰጥተዋል።
ስልጠናው በተለይ የምርምር ዘዴዎች ማሻሻያ (Research Methodology): ኳሊቴቲቭ እና ኳንቲቴቲቭ (Qualitative & Quantitative) የምርምር ዘዴዎችን በዘመናዊ መንገድ መጠቀም።
የመረጃ ትንተና ክህሎት (Data Analysis): በቱሪዝም ዘርፍ የሚሰበሰቡ መረጃዎችን በጥራት ለመተንተን የሚያስችሉ ሶፍትዌሮችንና ስልቶችን መጠቀም የሚያስችል ነው።
የኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር ዲን አቶ አህደር ጠና በበኩላቸው የልምድ ልውውጥ መድረኩ በሁለቱ ተቋማት መምህራንና ተመራማሪዎች መካከል የነበሩ መልካም ተሞክሮዎችንና የምርምር ውጤቶችን ማጋራት፣ ችግር ፈቺ ምርምሮች የሀገሪቱን የቱሪዝም ሀብት፣ የመስህብ ስፍራዎች ልማትና የእንግዳ ተቀባይነት አገልግሎት ጥራት የሚያሻሽሉ ጥናቶችን ማካሄድ ታሳቢ ማድረጉን ገልጸዋል።
ተቋሙ ከሀዋሳ ዩንቨርሲቲ ጋር በልዩ ልዩ መስኮች አብሮ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሞ ወደሥራ መግባቱ ይታወሳል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less