የሥልጠና ጥራትን ለማረጋገጥ የሁላችንም የጋራ ተሳትፎ ወሳኝ ነው ተባለ፡፡ ቱ.ማ.ኢ

November 02, 2026
የሥልጠና ጥራትን ለማረጋገጥ የሁላችንም የጋራ ተሳትፎ ወሳኝ ነው ተባለ፡፡ ቱ.ማ.ኢ

ጥቅምት 20/2019 ዓ.ም
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለአጠቃላይ ሠራተኞች ቀረበ።
በዕለቱ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንዳገለጹት፤ የሥልጠና ጥራትን ማረጋገጥ የምንችለው የሁላችንም የጋራ ተሳትፎ ሲኖር ነው። ይህንን ለማሳካትም ልምድ ማካፈል፣ እርስ በዕርስ መመካከር፣ እውቀትና ክህሎትን ማሳደግ፣ እንዲሁም የሥራ ብቃትና ቁርጠኝነት በኃላፊነት ስሜት መምራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመድረኩ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳግም አዲሱ የሩብ ዓመቱን ዕቅድ አፈጻጸም ዝርዝር ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን፤ በዝግጅት ምዕራፍ በነበረው አፈጻጸም አብዛኞቹ ግቦች ከዕቅድ በላይ መከናዎናቸውን ጠቅሰዋል። በቀረበው ሪፖርት ላይም ከተሳታፊዎች ጥያቄና አስተያየት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይከተሉ፡
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም፡ https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less