2019 ዓ.ም አዲስ ገቢ ሰልጣኞች ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

November 03, 2026
2019 ዓ.ም አዲስ ገቢ ሰልጣኞች ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

ቱ.ማ.ኢ
ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም
የፌደራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በ2019 የትምህርት ዘመን በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ለመሰልጠን የተመዘገቡ አዲስ ገቢ ሰልጣኞች ደማቅ የአቀባበልና የትውውቅ መርሃ-ግብር አከናወነ።
በመድረኩ የተገኙት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ለሰልጣኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያላስተላለፉ ሲሆን ኢንስቲትዩቱ በሀገሪቱ የቱሪዝምና የሆቴል ኢንዱስትሪ ውስጥ የሚታየውን የሰው ኃይል እጥረት ለመቅረፍና ጥራት ያለው ተግባር ተኮር ስልጠና ለመስጠት በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።
ሰልጣኞችም በተቋሙ የሚያስመዘግቡት ውጤት ለሀገሪቱ የቱሪዝም እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁመው ትምህርታቸውን በትጋት እንዲከታተሉም አሳስበዋል።
በተመሳሳይ የተቋሙ የስልጠና እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት ሰልጣኞች በተቋም ቆይታቸው ወቅት ስለሚኖራቸው ሁኔታና ስለሚሰጡት ተግባር ተኮር ስልጠናዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።
አክለውም ኢንስቲትዩቱ ዘመናዊ የስልጠና መሳሪያዎችን እና ብቃት ያላቸውን አሰልጣኞች በማዘጋጀት ሰልጣኞች በሥራው ዓለም ብቁ ሆነው እንዲወጡ ተስፋ ሰጪ ሁኔታዎች መመቻቸታቸውን አብራርተዋል።
በዕለቱ የመርሃ-ግብሩ አካል የሆነው የትውውቅ ስነ-ስርዓት የተካሄደ ሲሆን ዲኖች፣ ዲፓርትመንት ኃላፊዎችና መምህራን ራሳቸውንና የሚያስተዳድሯቸውን የትምህርት ዘርፎች ለአዲሶቹ ሰልጣኞች አስተዋውቀዋል።
በተጨማሪም ስለ ተቋሙ መመሪያዎች፣ ደንቦችና የህይወት ክህሎቶች ኦሬንቴሽን የተሰጠ ሲሆን፣ ተማሪዎች የትምህርት ገበታቸውን በሚገባ በመጠቀም ጥሩ ባለሙያ ሆነው እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less