ኢንስቲትዩቱ የሠራተኞቹን አቅም ለማሳደግ ያለመ የአቅም ግንባታ ስልጠና በተለያዩ ርዕሶች ሰጠ ።

November 02, 2026
ኢንስቲትዩቱ የሠራተኞቹን አቅም ለማሳደግ ያለመ የአቅም ግንባታ ስልጠና በተለያዩ ርዕሶች ሰጠ ።

ጥቅምት 21/2019 ዓ.ም
ቱ.ማ. ኢ
የፌደራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ለተቋሙ ሠራተኞች ሙያ ብቃትን እና ተቋማዊ አሰራርን ውጤታማነት ለማሳደግ ያለመ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
በዕለቱ ከተሰጡት ዋና ዋና የስልጠና ርዕሰ ጉዳዮች መካከል በዶ/ር ወርቁ ደጀኔ የቀረበው "ስርዓተ-ጾታ በተግባቦት ሂደት" (Gender in Communication) አንዱ ሲሆን፤ በስልጠናቸውም በተቋማዊ ተግባቦት ወቅት አጠቃላይ የጾታ እኩልነትን ያገናዘበ፣ አካታች እና ተገቢ የሆኑ የቃላትና የመልዕክት ልውውጦችን መጠቀም የሚያስገኘውን ጥቅም በሰፊው አብራርተዋል።
ስርዓተ-ጾታን ያገናዘበ ተግባቦት በተቋሙ ውስጥ ግልጽነትን ከመፍጠሩ ባሻገር፣ ጤናማና ፍትሃዊ የሥራ አካባቢን ለመገንባት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተመላክቷል።
በሌላ በኩል ደግሞ በዶ/ር ተስፋዬ ሄርጶ "የሙያ ስነ-ምግባር እና ተቋማዊ እሴቶች" በሚል ርዕስ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
ዶክተር ተስፋዬ በስልጠናቸው ወቅት እንደገለፁት፤ የስነ-ምግባር ደንቦችን አክብሮ መስራት የተቋሙን መልካም ስም ከማስጠበቁም በላይ ለአገልግሎት ፈላጊዎች ቀልጣፋ፣ ታማኝ እና ግልጽ አገልግሎት ለመስጠት መሰረት ነው፤ ይህም የተቋማዊ አገልግሎት ጥራትን ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግረዋል።
ስልጠናው በውይይትና በተሳታፊዎች ንቁ ተሳትፎ የታጀበ ሲሆን፤ የኢንስቲትዩቱ ሠራተኞችም ያገኙትን ግንዛቤ ወደ ዕለታዊ ስራቸው በመቀየር ለአገልግሎት አሰጣጡ ውጤታማነት በትጋት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less