የመንግስት ንብረት አስተዳደርን ለማጠናከር የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
ቱ.ማ.ኢ
ለፌደራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ሠራተኞች እና አመራሮች የመንግስት ንብረት አስተዳደር ህግጋት፣ ደንቦችና መመሪያዎች ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
ስልጠናውን የሰጡት ከፌደራል መንግስት ግዥእና ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን አቶ ዘነበ ገዛኸኝ ሲሆኑ፣ በንብረት አመዘጋገብ፣ አጠቃቀም፣ ጥገና እና አወጋገድ ዙሪያ ዝርዝርና ሰፊ ማብራሪያ አቅርበዋል።
አቶ ዘነበ ስለ መንግስት ንብረት አስተዳደር መታወቅ ያለበትን ሲጠቅሱ
ግልጽነትና ተጠያቂነት፡ የመንግስት ንብረት የህዝብና የሀገር ሀብት በመሆኑ እያንዳንዱ ንብረት በስርዓት እንዲመዘገብ እና ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንዲውል ያደርጋል፤
ብክነትን መቀነስ፡ ሀብትን በአግባቡ ከመጠበቅ ባሻገር አላስፈላጊ ብክነትንና ውድመትን በመከላከል የመንግስትን ወጪ ይቆጥባል፤
ዘመናዊ አሰራር፡ ንብረቶችን ከግዢ ጀምሮ እስከ መወገድ ባለው ሂደታቸው ህግን ተከትለውና በጥንቃቄ እንዲመሩ ያስችላል።
ስልጠናው የኢንስቲትዩቱን የንብረት አስተዳደር አሰራር ይበልጥ ቀልጣፋ፣ ግልጽ እና ውጤታማ ለማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋልም ተብሏል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less