የቱሪዝም ዘርፉን ዕድገትና ተወዳዳሪነት የሚያረጋግጠው አዲሱ ፖሊሲና የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሰጠ
ጥቅምት 26/2018 ዓ ም
ቱ.ማ.ኢ
የፌደራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከባህልና ቱሪዝም ሚንስቴር ጋር በመተባበር ለባለድርሻ አካላት አዲስ በጸደቀው የቱሪዝም ፖሊስ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
በመክፈቻ ፕሮግራም የተገኙት የባህልና ቱሪዝም ሚንስትር ዴኤታ አቶ ሰለሞን አየለ እንደገለፁት ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍና ሀገራዊ ሁኔታዎች ጋር የተጣጣመ፣ የቱሪዝም ዘርፉን ሁለተናዊ ዕድገትና ተወዳዳሪነት የሚያረጋግጥ አዲስ የቱሪዝም ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር ሲገባ፣ ፖሊሲውም ሰፊና የተለያየ የቱሪዝም ሀብትን በአግባቡ በማልማት የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት ማፋጠን ላይ ያተኮረ መሆኑ ታውቋል።
ይህ አዲስ ፖሊሲ በፌዴራልና በክልል ተቋማት፣ በግሉ ዘርፍ፣ በሙያ ማህበራት እና በሌሎችም ባለድርሻ አካላት መካከል ጠንካራና የተቀናጀ ትብብር እንዲኖር በማድረግ ረገድ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።
የፖሊሲውን ዓላማዎችና አቅጣጫዎች ከግብ ለማድረስ እና በዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመሙላት የባለድርሻ አካላት ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን የገለጹት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሰለሞን አየለ፤ ለዚህም ስኬት የባለሙያዎችና የኃላፊዎች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አመላክተዋል። ስልጠናው ፖሊሲውን ከመሬት አስነስቶ ወደ ተግባር ለመተንተንና ዘርፉን የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ዋና ምሰሶ ለማድረግ የሚያስችል ጠንካራ መሠረት የሚጥል መሆኑን ተናግረዋል ።
በመርሐ-ግብሩ ላይ የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው በትብብር በመስራት ሀገሪቱ ከቱሪዝም ማግኘት የሚገባውን ጠቀሜታ ማግኘት እንደሚቻል በመግለጽ ሰፊ ማብራሪያዎችን ሰጥተዋል። እንዲሁም የቱሪዝም ከፍተኛ ባለሙያዎች ስለቱሪዝም አመጣጥና አጀማመር ሰፊ ገለጻ አድርገዋል።
ይህ አጠቃላይ አቅም ማጎልበቻ ስልጠና በፌደራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በEASTRIP ፕሮጀክት ድጋፍ የተካሄደ መሆኑ ተገልጿል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less