በቱሪዝም ፖሊሲ ዙሪያ ሲሰጥ የቆየው የአሰልጣኞች ሥልጠና ተጠናቀቀ

November 09, 2026
በቱሪዝም ፖሊሲ ዙሪያ ሲሰጥ የቆየው የአሰልጣኞች ሥልጠና ተጠናቀቀ

ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በአዲሱ የቱሪዝም ፖሊሲ ዙሪያ ሲሰጥ የቆየውን የአሰልጣኞች ሥልጠና አጠናቋል።

በEASTRP ፕሮጀክት ድጋፍ የተዘጋጀው የአራት ቀናት ሥልጠና፣ የቱሪዝም ፖሊሲውን ከሰነድ ወደ ተግባር በማሸጋገር የፖሊሲውን ዓላማዎችና አቅጣጫዎች በተለያዩ የትግበራ ደረጃዎች እንዲሰርፁ ለማድረግ ያለመ ነው።

በሥልጠናው የተሳተፉ አሰልጣኞችም በየክልላቸው ወደሚገኙ ተዋረዳዊ መዋቅሮችና የቱሪዝም ዘርፍ ባለድርሻ አካላት በማስፋፋት የፖሊሲውን ይዘት፣ ዓላማና የትግበራ አቅጣጫዎች የማድረስ ኃላፊነት ይኖራቸዋል።

ለተጨማሪ መረጃ፦

🌐 www.visitethiopia.et

🌐 http://mot.gov.et

Telegram: https://t.me/tourismethiopia

Facebook: https://web.facebook.com/

t.me/ethiopialandoforigins See less