በቱሪዝም ማሰልጠኛ የተቋቋመው የኢንዱስትሪ ቴክኒካል አማካሪ ቦርድ የውይይት መድረክ አካሄደ።
ጥቅምት 28/2019 ዓ ም
መንግስት ለሀገራችን ኢኮኖሚ እድገት የቱሪዝም ዘርፍ የሰጠውን ልዩ ትኩረት ተከትሎ፣ የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በአዲስ መልክ የተቋቋመው የኢንዱስትሪ አማካሪ ቦርድ ትውውቅ እና የተከናወኑ ሥራዎችን የመገምገሚያ መድረክ አካሂዷል።
በመድረኩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ፣ መንግስት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት አፅንኦት በመስጠት ሀገራዊ ኃላፊነቶችን በብቃት ለመወጣት ሙያዊ ድጋፍ ማድረግ የሚችሉ ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ መስራት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።
የስልጠና ጥራትና ተደራሽነት፡ ለመጨመር የቱሪዝም እና ሆቴል ዘርፍ ሙያዊ ስልጠናዎችን ጥራት፣ ተገቢነትና ተደራሽነት ለማረጋገጥ ተቋሙ ተከታታይ ሥራዎች መስራቱን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
አቶ አብርሃም ለገሠ በበኩላቸው ለአማካሪ ቦርዱ እየተከናወኑ ዋና ዋና ሥራዎችን በዝርዝር አቅርበዋል፤ በተለይም
የስልጠና ጥራትና ተደራሽነትን በተመለከተ የቱሪዝም እና ሆቴል ዘርፍ ሙያዊ ስልጠና፣ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ፣በመሠረተ ልማት ግንባታ እንዲሁም የአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ሽግግር ሰፊ ርብርብ እየተደረገ መሆኑ ገልጸዋል።
ከዚህም ባሻገር የባለድርሻ አካላት ተሳትፎን በተመለከተ የዘርፉን ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ጥረትና የባለቤትነት ስሜት ወሳኝ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል የሚገባው መሆኑን በመድረኩ ተገልጿል።
ከጥናትና ምርምር ዘርፍ አቶ አህደር ጠና ባቀረቡት የሰልጣኞች ስምሪት ዳሰሳ ጥናት (Tracer Study) የኢንስቲትዩቱ ምሩቃን 82% ሥራ ላይ መሆናቸውና ከዚህም 78% ሴቶች መሆናቸውን አመላክቷል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less